=<({አል-ኢኽላስ 112:1-4})>=
ﺑﺴﻢ ﺍﻟﻠﻪ ﺍﻟﺮﺣﻤﻦ ﺍﻟﺮﺣﻴﻢ
1. በል! እርሱ አላህ አንድ ነው።
2. አላህ (የሁሉ) መጠጊያ ነው።
3. አልወለደም፤ አልተወለደምም።
4. ለእርሱም አንድም ብጤ የለውም።
![]() =<({አል-ቁርአን 96:1-5})>=
![]() በቡኻሪ በተዘገበው ሐዲስ መሰረት እውቀትን መሻት በእያንዳንዱ ሙስሊም ላይ ግዴታ ነው። ![]() |
---|
{The Believing woman is Alert!!!}
አማኝ ሴት ንቁ ናት(ማንቂያናት)::
بسم الله الرحمن الرحي
አንደኛዉና ዋነኛዉ አማኝ ሴትን ልዪ የሚያደርጋት ባህሪያቶች በአላህ ያላት እምነት፤የፀና እምነቷ በዚህ አለም የተከሰተዉ ቢከሰት መጥፍ አጋጣሚወች ቢፈጠሩ በአላህ ፍቃድ ነዉ የምትል የሆነች ናት::
የትክክለኛ ሙስሊም ሴት እምነቷ ወይም አቂዳዋ ንፁህ እና ግልፅ ሲሆን በድንቁርና እድፍ፣በተሳሳተ አመለካከት እና ጥንቆላ ያልተበከለ ወይም ያልተመረዘ የሆነ ነዉ::እምነቷ ያአላህን እምነት መሠረት ያደረገ፣አንድነቱን፣ከሁሉ በላይ መሆኑን፣ዘላለማዊነቱን፣ሁሉን ማድረግ የሚችል መሆኑን፣ሙሉ አለምን ተቆጣጣሪ እና ሁሉም ነገር ወደርሱ ተመላሾች መሆናቸውን በማመን ነዉ::
{Al Quran 45:26}
"say:It is Allah who gives you life,then gives you death;then He will gather you together for the Day of Judgement about which there is no doubt,but most men don't understand."
ትክክለኛ ሙስሊም ሴት ጌታዋን በትጋት ታመልካለች።እንዲሁም እስላማዊ ግዴታዋን ያለምንም ቸልተኝነት ትወጣለች
{አዘዉትራ በቀን አምስት ጊዜ ትሠግዳለች}
ሶላትዋን በተደነገጉት የሶላት ሰአቶች ትሰግዳለች።የቤት ዉሰጥ ስራ ወይም እንደ ሚስትነት እና እንደ እናትነት ያለባት ግዴታ ይህን ከማድረግ አያግዳትም።
ሶላት በአላህ እና በባሪያዉ መካከል ያለች መገናኛ(link) ናት።
ሶላት የጥንካሬ፣የፅናት፣የምህረት፣የደስታ እና የሀጢያት እድፍን ማስወገጃ መሳሪያ ናት።
ስለዚህ ዉድ ሙስሊም እህት ወንድሞቸ ጊዜዉ ሳይጨልምብን የሞትን ቅጣት ከመቅመሳችን በፊት አሁኑኑ ወደ አላህ እንመለስ!!!
የወጣቱ ተልዕኮ አድራሻ
ኢስላማዊ መጽሐፎችን ያውርዱ |
---|